Eshete Kassa ከጠላት ምንም ነገር መዋስ አያሻም

==========================
የዘር ፖለቲካ የሕወሓት ፖሊሲ የመለስ ዜናዊ ዶክትሪን ነው
ሚኒሊክ አደረሰው ከሚባለው ይልቅ በ27 ዓመታት ሕወሓት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በኦነግ ሥም የተገደሉት የኦሮሞ ወጣቶች ቤት ይቁጠረው የኦሮሞ ሪሶርስ የተቦጠቦጠው በሕወሓት ዘመን ነው
ግን ዘረኞች ሕወሓትን አይጠሉትም እንደ አጋር ይቆጥሩታል የአይዲዮሎጂ አባት ተደርጎም የወሰዳል” የመለስ ራዕይ”
የኦነግ እና የሕወሓት ገብቻም ከዚህ ርዕዮት አለም የተነሳ ነው
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የጀርመን ናዚ አይሁዳውያንን በዘራቸውና በዕምነታቸው ለይቶ ለማጥፋት ሞከረ
ከ6 ሚሊየን በላይ አይሁዳውያንን በዘግናኝ ሁኔታ ጨፈጨፈ

እስካሁን በዓለም ታሪክ በሰው ዘር ላይ የተፈፀመባቸው ሰበአዊ ወንጀል እንደ አውሮፓ አይሁዳውያን በታሪክ የለም

ግን አይሁዳውያን ከጠላት በተቃራኒ እንጅ ጠላት ላይ ምንም የወረሱት የለም

እንዲያውም የጠፉበት ምክንያት ዕምነታቸውና ዘራቸውን የበለጠ አጠናክረው በዓለም ኃያል ሁነው ዘልቁ እንጅ ዕምነታችን እና ዘራችን ነው ለዚህ የዳረገን ብለው ከማንነታቸው አላፈገፈጉም

ወደኛው ወደ ራሳችን ስንመጣ ደግሞ ከገዳያችን ከጠላታችን የተዋስነውን ልምድ ከሕወሓት ውድቀት በኇላ ያነውን በትግርኛ ከነበረው ወደ አማረኛ ብቻ በመቀየር ጥላቻ ማግለልን እንደ ትግል ስልት ያደረገ የአማራ ብሔርተኝነት በሚል ሽፋን እየተሠራ ያለው ነገር አሳዛኝ ተስፋ አስቆራጭ ከአንድ የክፉ ታሪክ አዟሪት ወደ ሌላ እርስ በርስ የወንድማማች ጦርንት የሚከት ነገር እያየሁ ነው
አያት ቅድመ አያት የተዋደቁላትን ኢትዮጵያ የመጠበቅ ኃላፊነትን በሕወሓት የ27 ወይም የ40 ዘመን እኩይ ዓላማ ምክንያት አማራ የአባቶቹን አደራ መካድ የለበትም
የዘር ፖለቲካ መዘዙ በመጨረሻው ቀን ለክ እንደሕወሓት አወዳደቁ የከፋ ነው
ሕወሓት ለትግራይ ሕዝብ ልዐለና እንዲሁም ነፃ ላወጣ እያለ ነበር ነገር ለትግራይ ሕዝብ ያመጣለት ነገር ጥላቻን ነው የትግራይ ሕዝብ በሕወሓት ምክንያት ከሌላው ወገኑ ጋር አብሮ እንዳይቆም አድርጎታል
ሕወሓት ሲዘርፍ ሲሰርቅ ሲገድል ሲያስገድል ሲያፈናቅል ሲያሰድድ በትግርኛ ቋንቋ ተጠቅሞ እኛ ትግሬዎች እንዲህ ነን እያለ ነው ።
በሕግ ከለላ ሥር ታሰረዋል የተባሉት የትግራይ ተወላጅ ባልሆኑት በብዛት የአማራ እና የኦሮሞ ታሳሪዎች ላይ ግድግዳ ግፉ ይባሉ ነበር በመጨረሻም እኛ ትግሬዎች እንደዚህ ግድግዳ ነን የምታመጡት ነገር የለም ይባሉ ነበር የትናት ትዝታ ነው

አማራ በሕወሓት ጠላት የተባለው አማራ በትግሬ ላይ ተከዜን ተሻግሮ የፈፀመው አንድም ጥፋት አልነበረም
በተቃራኒው በተለየይ በጎንደር የምናውቀው ከተከዜ ማዶ ለሚመጡት የትግራይ ሰዊች ከቤቱ አሳድሮ አግር አጥቦ ከመኝታው ለቆ አስተኝቶ ሲሀፀዱመ ስንቅ ሰጥቶ በፍቅር የሚቀበል ነበር
በሕወሓት ዘመን ያን የመሰለው ውለታ ተረስቶ ከተከዜ ማዶ የሰለጠኑ ሚሊሻዎች በሕወሓት እየተላኩ በሌሊት ወገንን ከየቤቱ እየታፈኑ ደበዛቸው ጠፍቶ የቀሩ አያሌ የሰሜን ጎንደር ሕቦች እንዳሉ ይታወቃል
አማራ እንዲጠፋ በዘረኞች የተወሰነው አማራ ኢትዮጵያን ስለሚወድ ብቻ ነው
አማራ በትግሬው ነፃ አውጭ ሕወሓት ጠላት የተባለው አማራ እያለ ኢትዮጵያን ማጥፋት የማይችል መሆኑን በመረዳቱ ነው ።
የህ ነው የአማራ ሞት ስቃይ ሰደት እስራት ግርፋት መፈናቀል መወክንያት!
ኢትዮጵያን ለማፍረስ በመጀመሪያ አማራን ማፍረስ ወይም ማዳከም
ይህ ነው ዋናው ነጥብ

ከዚህ ላይ ስለጀርመን ናዚዎች የወንጀል ታሪክ ለማውራት አይደለም የኔ አላማ

የአይሁዳውያኑን ታሪክ በመጠኑም ቢሆን የአማራ ሕዝብ ሊማር የሚችልበትን ዘዴ ለመጠቆም ነው

በመለስ ዜናዊ የተመራው ሕወሓት ከመነሻው እስከመድረሻው ዓላማየ ብሎ የትግሉ አርማ አድርጎ የተነሳው በአማራ ዘር ላይ ብቻ ነው
“አማራ ጠላት ነው ስለዚህ መጥፋት አለበት ” ሕወሓት
ከዚህ ላይ ወደ አማራ ሕዝብ ልመለስ ሕወሓት ለትግሉ ማኒፌስቶ ሲቀርፅ በግልፅ አማራ ጠላት ነው ብሎ ማስቀመጡ የአደባባይ ምስጢር ነው
ከ40 ዘመን በላይ በተግባር የፈፀመውም እንደ ጀርመን ናዚዎች ተመሳሳይ ነው ለአማራ የሚራራ ልብ የላቸውም የሕወሓት ገዳይና አፋኝ ግሩፕ
በየማጎሪያ ቤቱ ከአፋቸው ከሚወጣው እጅግ ቀፋፊ ስድብ ጀምሮ እስከ ድብደባውና ጭካኔው
እሴቶች በዘር ብልታቸው በማህፀናቸው ባዕድ ነገር መጨመር እስከወንድ ብልት ማንኮላሽትና ኩላሊትና ስስ አካላትን በድብደባ ምክንያት እንዲመረቅዝ እና ጤናቸው እንዲታወክ በማድረግ በድብዱባ ብዛት ሕይታቸው እንዳያልፍ ሰው ሰራሽ ድህነት ብዙኃን የአማራ ገበሬ በረሀብ እንዲያልቅ
ዘሩን እንዳይተካ አማራ የመውለድ ፀጋውን በመንፈግ በዘመቻ መልክ አማራ እሴቶች ተገደው የአምክን መርፌ እንዲወጉና ጤናቸውም እንዲታወክ የጤን ኤክስቴንሽን በሚባል ሽፋን ካድሬን በአማራው ሕዝብ በማሠማራት የሚችሉትን ያክል ስልታዊ የዘር ማጥፋት ተፈፅሟል
ከዚህ ባሻገር ደግሞ አማራ ጠላት ነው ተብሎ በትምህርት ካሬኩለም መመሪያ ወጥቶ በኢትዮጵያ ምድር አማራ ተቀባይነት እንዳይኖረው ተደርጎ አማራ ብዙ መከራ ከመቀበልም በላይ እንደዶሮ አንገት በመቅላት እንዲገደል ሕወሓት ይሄን አድርጏል አሁንም በየአካባቢው የሚፈፀሙት አረመኔያዊ ግድያ በቡራዩም ጭምር ያየነው የሕወሓት የእጅ ሥራ ነው
ይህ በዚህ እንዳለ ነው እንግዲህ
በዘረኞች ይህ ሁሉ መከራ የተፈፀመበት ሕዝብ ከጠላቱ ከመለስ ዜናዊ ልምድ በመቅሰም ሳይቀነስ ሳይጨመር በማንነቴ እየተባለ እንደቀልድ የተጀመረ ጨዋታ ዛሬ ላይ በአማራው ሕዝብ ያነኑን የሕወሓት ሌጌሲ ለመጫን ልክ በሕወሓት ዘመን የነበረው ጥላቻ እኔ ብቻ ልወቅልህ የሚሉ ስለምን እንደሚታገሉ ማነን እንደሚታገሉ በውል ማስረዳት የማይችሉ ታላቁን የአማራ ሕዝብ በማደናገር ላይ ናቸው

Image may contain: 1 person