Image may contain: 6 people, people smiling

ይድረስ ለክቡር ጠ/ሚ ለ ዶ/ር አብይ አህመድ

የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ እና የ አርበኛ አቶ አጎናፍር ገ/መድህን የኢትዮጵያ አርበኛች ባለውለታ ልጆች: –

1. ወንደሰን ተሰማ
2. አለማየሁ ተሰማ
3. ምኒልክ ተሰማ
4. ዳንኤል አጎናፍር

አራቱም የ አክስታማማች ልጆች ሆኖም ግን አብሮ በማደጋቸው እንደወንድማማቾች የነበሩት እነዚህ ወጣት ኢትዮጵያን የ ዛሬ 24 ዓመት በ ደህንነቶች ታፍነው የት እንደደረሱ ሳይታወቅ ይህው 24 ዓመት አለፋቸው ።
የ ወንደሰን ፣ የ አለማየሁ ፣ የ ምንሊክ እናት ፣ ወ/ሮ ተሰማሽ ወንድምአገኘሁም ሶስት ልጆቻን እና የ ታናሽ እህቷ የ ወ/ሮ ጌራወርቅ ወንድምአገኘሁ ልጅ ዳንኤል የት እንደደረሱ ሳታውቅ ከዚህ ዓለም ተለይታለች ።
እንዲሁም አርብኛ አቶ አጎናፍር የ ልጃቸውን የዳንዔል እና እንደ እራሳቸው ልጆች የ ሚያዩዋቸውን ሶስቱን የ እውቁ አርበኛ ደጃዥማች ተሰማ እርገጤ ልጆች የትእንደደረሱ ሳያውቁ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል ።

በ አሁኑ ሰዓት የ ዳንኤል እናት ፤ የእነ አለማየሁ ፣ ወንድወሰን እና ምንሊክ አክስት ወ/ሮ ጌራወርቅ ወንድምአገኘሁ ፦ ዛሬ ከነገ ይገኙ ይሆን እያለች በችንቀት በለቅሶ በሃዘን ስትሰቃይ ይህው 24 ዓመት አለፈው ።
የ እነዚህ ንፁዋን ዜጎች አላንዳች በደል በ ደህንንነት ታፍነው መሰወር መላ ቤተሰቡን እጅግ የከፋ ሀዘን ላይ ከጣለው ይህው 24 ዓመት እለፈው ።
ያልተገባበት ቢሮ ፣ ኣቤት ያልተባለበት ቦታ የለም ።
ሆኖም ግን እስከዛሬ ቀን ድረስ አንዳንች ፍንጭ የሚሰጥ አካል አልተገኘም ።

አሁን ቤተሰቡ ክቡር ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር ዓብይን የምንጠይቀው ፡
እነዚህን የአገር ባለ ውለታ የ ሁኑትን አርበኞች ( ደጅአዝማች ተሰማ እና አቶ አጎናፍር ) ክብር ሲሉ ጉዳዩን እንዲመለከቱልን እና ልጆቹ የት እንደደረሱ የ ደህንነት መስርያቤቱን እንዲጠይቂልን በ አክብሮት እንጠይቃለን ።

በዚህ አጋጣሚ ከ እንዚህ ልጆች ጋር በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች የት እንደደረሱ እንዲጣራ እንጠይቃለን ።

የ ሰው ልጅ ወደዚች ዓለም ሲመጣ ነፃ ሆኖ ነው እና
ማንኛውም ሰው በዚች ዓለም ሲኖር ነፃ ሆኖ ይኑር ።