የውጭ ምንዛሬ የህወሓት ስስ ብልት!!

#StarveTheTPLFBeast  |  #ጉጅሌህወሓትንአንቀልበው  | #BulguuHinHoratin

 

የውጭ ምንዛሬ እጥረት የህወሓት አገዛዝ ቁጥር አንድ ራስ ምታት ነው፣ ወያኔንም ይበልጥ የምናዳክምበት ስስ ብልት ነው።አማራጭ ፈልጎ በመላክ በመቀነስ ወይም ከተቻለለ ተወሰነ ጊዜ በማቆም የዘራፊውን ቡድን የኢኮኖሚ መሰረት ማናጋት ይችላሉ። የወቅቱን የዶላርን እጥረት ከጥቁር ገበያና ፣ነጋዴዎች ምንዛሪ ወደ ዱባይ ከማሸሻቸው ጋር ማያያዝ ከተጠያቂነት ለመሻሽ የሚደረግ ቅጽበታዊ መፍጨርጨር ነው።ለዶላር እጥረቱ ዋናኛ ምክንያት ወያኔ አብዛኛውን የምንዛሪ ክምችት ለዘራፊው ኤፈርት እና ለጨፍጨፊው መከላከያና ደህንነት ሃይሉ በመጠቀሙ ብቻ ነው።

የበለጠ የሬሚታንስ / ሃዋላ ተአቅቦ ማድረግ ማለት የወያኔን ዘራፊና ጨፍጫፊ ተቋማት ማዳከም ማለት ነው።