ይድረስ ለተከበሩት ኢ/ ር ይልቃል ጌትነት
===================[[[[[====
ወንድም ይልቃል ጌትነት

አንተ ያሳለፍከውን ያክል ባላሳልፍም አንተ የሚደርስብህን ወከባ በኔ ላይ ባይደርስም
በመጠኑ ይገባኛል ።

ግን ሰው እንዳኖሩት አለመገኘት ግን ግራ ያጋባል ።

ወንድም ባለንጀሮችህን የቀማህ ማነው?

ግማሾችን በመግደል እንደ እነ ወጣት ሳሙኤል አወቀ የመሰሉትን።

ግማሾቹን በማሰር እንደ እነ ዮናታን ተስፋዬና ሌሎቹንም ።
የተቀሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አብዛኛዎቹን ያሰደደው ማነው ንገረኝ ልጠይቅህ?
በኦነግ ሳይሆን በሕወሓት ነው ።

በምን መለኪያ ነው እነ ለማ መገርሳ ከሕወሓት እኩሉ ተፈርጀው መቅረባቸው?

ወንድም ዛሬ ላይ የኦነግ ከሳሽ ሁነህ የቀረብከው ለአማራ መቆርቆርህ ነው ?
ወይስ በቅርቡ የታየህ ነገር አለ?
ከሆነ ጋሬ ለመፈናጠጥ ነው?

የኢትዮጵያ ችግር ምንጩ #ሕወሓት እና #ሕወሓት ብቻ ነው ሌላውን መወንጀል የግፍም ግፍ ነው።

ወንድም ይልቃል

አቶ ለማ መገርሳ ኢትዮጵያ ማለታቸው ነው እረፍት የነሳህ ወይስ ከዚህ በኋላ ምን ይፈጠራል ብለህ ስለተጨነቅህ ነው ።

ሕወሓት ሕወሓት ነው አማራም አማራ ነው ።
አማራ መገደሉ ብቻ ሳይሆን እጅና እግሩ የታሰረ አቅመ ቢስ እሩጫውን በፀረ አማራው ብአዴን የተቀማ ነው ።

አያግዘነም የራስን ጉድፍ ከዓይን ሳናወጣ የሕወሓትን ሥልጣን የሚገዳደር ፈታኝ ወቅት ሲመጣ ልንደሰት ይገባል እንጅ ሲሆን በወጣይ አብረውን ከሚኖሩት ከሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ራስ ላይ መሰቀል ወደድንም ጠላንም አቅም የለንም ?
አንድነት መልካም ነው ግን የአንድነት ደጋፊ የሚባለው ራሱን እንኳ አንድ ለማድረግ የዝብሪት ደጅ ሳይዘጋ ያድራል እንዲሉ ።
አንድነት ብለው በሁለ ገብ ትግል ለመረጡት ድጋፍ የነፈግን ተቀምጦ እዬዬው አይገባኝም ለኔ።

አይምሰልህ በአማራ ጭፍጨፋ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ብቻ መወንጀሉ ትግልህ ምን ለማምጣት እንደሆነ አልገባኝም የኦሮሞ ሕዝብ መብት አለው የመጠየቅ ።

እኛ የራሳችን መብት በሕወሓት ተነጥቀን ትንሹ ድኃ ትልቁን ድኃ አይወደውም እንዲሉ የኦሮሞን ፖለቲከኞች የግብረ ገብ አስተማሪ ልንሆን አይገባም ።

እኛ አንደበታችን የተዘጋው በፀረ አማራው ብአዴን ነው ፣ ለብ በል ብአዴን ከበስተጀርባው ማነው ታዋቂው ጆሴፍ ጎብልስ በረከት እኮ ነው ።
#ብአዴን
አዲሱ ለገሠ በረከት ስምዖን

በዚህ ሰዓት አንተ ማነህ?
ሌሎቹን ለመክሰስ አትችልም አቅመ ቢስ እኮ ነህ የሁለ ገብ ትግልን ትጠየፋለህ መሳሪያ ናፋቂም ብለሀል ።
አቶ ለማ መገርሳ ማድረግ የሚችለውን እየሞከረ ነው የኦሮሞን ሕዝብ ከደገፈው
ሊሳካላት ይችላል።
እኛ እኮ ምላስ ብቻ ነው የቀረን ተስፋ ሰጭ ነገር አላይም ውሉ የጠፋበት የተበተነ ሕዝብ ሁነናል ።

ስማኝ ወንድሜ ያልታየህ ነገር አለ
አማራ በኦሮሞ ብቻ አይደለም የሚገደለው በቤንሻንጉል የተጨፈጨፉት በማን ነው?
አስከሬናቸው እንዳይለቀም ብአዴን ማገዱንስ አልሰማህም?

ብአዴን የአማራ የሆነውን ሁሉ ቆሞ ለትግሬ ያስረክባል ብአዴን የጎንደርን መሬት ወልቃይት ጠገዴን ጠለምትን ከዋልድባ ገዳም ድረስ አስረክቧል በቅርቡ
#ገዱ_አንዳርጌ ብቻውን የቆላ ወገራ የግጨውን ምድር በፊርማው አስረክቧል ።
በጎጃም የመተከል አውራጃን ለትግሬ ልዩ ግዛት ቤንሻንጉል በሚል አዲስ ሀገር በቅርቡ ነፃ የምትወጣ ሀገር ፈጥሯል ።

ብአዴን የሕወሓት ሥራ አስፈፃሚ ሁኖ ይሠራል በዋልድባ ገዳም ደናግል መነኮሳት አማራ በመሆናቸው ብቻ በምንኩስና ስማቸው ሳይሆን በአለም ስማቸው እየተጠሩ ወደጫካ እየተወሰዱ በግሩፕ በትግሬ ታጣቂ ተደፍረዋል።
የወልድባ መነኮሳት አማራ በመሆናቸው ተገድለዋል ተገርፈዋል ማዕከላዊ ሳይቀር በጨለማ ታስረዋል ቶርችም ተደርገዋል
ብአዴን የአማራ ተወካይ ከሆነ ምን ይሰራል?

እውነት እውነት እልህ አለሁ
ከሕወሓትም ከኦነግም ከኦህዴድም በላይ ብአዴን የአማራ ጠላት ነው!

#ብአዴን ማለት —#በረከት_ስምኦን አዲሱ ለገሰ ማለት ነው።

የአንድነት ኃይል የሚባሉትን ኢትዮጵያ ታገባኛለች የሚሉትን ምሁራን በጋጠ ወጦች ሲያሰድብ የሚውለው እኮ ብአዴን ነው ።
ስለኢትዮጵያ የአቅማቸውን የሚሰሩትን በአማራ ስም አደራጅቶ ሲያሰድብ የሚውለው በማሕበራዊ ሚዲያ ከሕወሓት በተዘጋጀ ፕሮግራም በብአዴን አስፈፃሚነት በኮድ ስም በመጠቀም አማራ አማራ እያሉ ድርጅት በማፍረስ ለተጎዱት ሕዝብ ተሰባስበን እንዳንወያይ ባንድ እንዳንቆም እያደረጉን ያሉት እኮ የሕወሓት ብአዴን በኩል ተመልምለው በቂ ስልጠና ተቀብለው የተበተኑ ዕጓለ ማውታ ናቸው ።

ግን የአንድነት አቀንቃኝ የኩሩ ፖለቲካ አር እና ቆሻሻ እየተቀባ ተዋቸው የሚል ነው ።
ለምሳሌ እንውሰድ
#አቶ_ተክሌ_የሻውን
ተግባር እንየው

አማራ ብለው መጮህ ከጀመሩ ጊዜው ረዥም ነው ግን ለአማራ በሚጠቅም አብሮ ለመሥራት ሳይሆን ሕወሐሰት አጥብቆ የሚጠላቸውን በመጥላት ነው መከፋፈል ነው
ከ20 ዓመት በላይ ነው እነ ታማኝ በዬነን
ፕ/ ር መስፍን ፕ/ ር ብርሃኑ ነጋን እና ሌሎቹን ያለማቋረጥ በመስደብ ላይ የኖሩት አሁንም ያሉት ።

በዚህ ወቅት በብዙህ ሽህ ሁነው ስማቸው ኮድ የተደረገ የትግረሰይ ሰው የተመደቡበት የአንድነቱን ኃይል ኢትዮጵያ የሚለውን እያጠቁ ያሉበት ነው ።
ቤተ ብአዴን አማራውያን ከፊት ለፊት የቆሙት ጥቂት በጣት የሚቆጠሩ አስር የማይሞሉ ናቸው ።
እኒህ የብአዴን ሰዎች አንደነቱን ለመጉዳት የኦሮሞን ሕዝብ በአማራ ሕዝብ ሥም ተጠቅመው ኦሮሞን ሲሳደቡ እናያለን ።
#ወንድም
ያንተው በትር የተነሳው ደግሞ በኦሮሞው ላይ ነው ።

ስለዚህ ሕወሓትን ከምንም ጋር አላወዳድረውም ሕወሓት በዓለም ከዚህ በፊት ያልነበረ ወደፊትም የማይኖር የራሱን ሀገር ለማፍረስ ስንት ርቀት የተጓዘ አደገኛ ቡድን መሆኑ ግልፅ ነው።

ወንድም ሰይፍህን ወደ አፎቱ መልሰው ትግሉ እንደዚህ አይደለም
ሕወሓት ከዚህ ባለፈ አማራን ወደ ጅምላ መግደያ ካንፕ አስገብቶ የጅምላ ጭፍጨፋ ለማድረግ ዕቅድ አለው እኛ ደግሞ የጠላትን የጥላቻ ደረጃ በውል የተረዳን አንመስልም ።
ጥርሱ ገጦ የሚታዬን ኦነግ ነው ።
ይህ ክፉ ምስል በአማራው እንዲቀረፅ ያደረገው መለስ ዜናዊ ነው በምዕራብ ሐረርጌ አማሮችን በኦነገረ ሥም ያሳረደው ከዛም ያለማቋረጥ በፕሮፖጋንዳ የተሰራው ነው ።
ኦነግ ባሕርዳር ደሴ ጎንደር ጎጃም
ላይ እንደ ህውሓት በጠራራ ፀሀይ በስናይፐር አልገደለንም ።
የሚገድሉን እኮ ሕወሓትና ብአዴን ናቸው ።
የአማራ ሕዝብ ከብአዴን ነፃ ካልወጣ የቱን ያክል ቢፈራገጥ ለነፃነቱ አይበቃም ።
ሞት ለቅጥረኛ ሕሊና ቢሶች