ሕወሀት የቆየ ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ
===========================
ሕወሀት የአማራውን ሕዝብ አዳክሞ ለማጥፋት የቆየውን እቅዱን በጥንቃቄና በኛው በራሳችን እየተጠቀመ ነው ።16299008_10208283294261071_1127915483294565266_n
የኛ የምንላቸው ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ሕወሀት የጋራ ጠላት ሁኖ ሳለ ባንድ ላይ ከመቆም ይልቅ ሕውሀት የሚፈልገውን ለሕወሀት የሚጠቅመውን እየሠሩ እያየን ነው።
ሕወሀት ችግር ፈጥረውብኛል የሚላቸውን እኑሱን አሸባሪ ፀረ ልማት ወዘተ እያለ ሕግ እስከመቀየር ደርሷል ።
ታዲያ ይህንን ነው የኛ የምንላቸው በኛው ሥም እየተንቀሳቀሱ ለሕወሀት እጅግ ጠቃሚ የሆነ ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙት ።
ሕወሀት የኢሳት ሚዲያን ከአየር ለማውረድ ባደረገው ዲፕሎማሲያዊና የፈንድ አቅም ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት በመቆጣጠሩ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይን አፍስሶ #ከ20 ጊዜ በላይ #ኢሳትን ከአየር እንዲወርድ አድርጓል ሁኖም ግን ኢሳት በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥረት እነሆን አፈናውን ተቋቁሞ #ከ6 ዓመት በላይ እንደቀጠለ ይገኛል ።
ሕወሀት በዚህ ወቅት የታወቀውን አማራን ለማዳከም ዕቅዱ ይረዳው ዘንድ #ጎንደርን ለመሰንጠቅ #የቅማንትን አጀንዳ በአዲስ መልክ በሕወሀት #ብአዴን ምስለኔኔዎች ወደተግባር የገባበት መሆኑ እየተነገረ ነው ።
@ታዲያ ለዚህ ወያኔ ሕወሀታውያን ሥራ እየረዱና የቅደመ ዝግጅት መንገድ የጠረገበት የኛ በምንላቸው በራሳችን ሰዎች ነው ።
በጎንደር የሕወሀት ጭቆና ያስመረራቸው ወጣቱና ገበሬዎች በቃን ብለው ሲነሱ አማራን እናደራጅ በሚል ሽፋን ከሀገር ውጭ በሚኖሩ ብቸኛው አማራ ነን በሚሉ ንቅናቄው ተጀመረ መደራጀቱ ባልከፋ ነበር የጀፋው ነገር ለመደራጀት የሄዱበት መንገድ ለአማው ስቃይና በደል ለማላቀቅ ሳይሆን ለተጀመረው ንቅናቄ በጋራና በሌሎች የትግል አጋር ጋር እንደ አንድ የትግል አጋር መውሰድ ሲገባቸው የዛን የገበሬውን እና የሌሎች አካላትን በጋራ መሥራት ለመነጠል በጣም በዘቀጠ የጥላቻ ቅስቀሳ በማድረግ የገበሬውን ዓመፅ እስከማወክ የተሄደበት ተግባር ነው ።
በተለይ ስለአማራው ሕዝብ ስቃይና ያንዣበበትን አዳጋ ለሕዝብ በማሰማት የታወቁት ግለሰብም ጭምር አውቀው ይሆን ሳያውቁ በዚህ ሰዓት በየአደባባዩ እየሰሩት ያለው እጅግ ለአማራው ከሕወሀትም በላይ ተጨማሪ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮችን ሲነናገር ይሰማሉ ።
ለምሳሌም
========
አግ7 — ፀረ አማራ
የኢሳት ሚዲያ— ፀረ አማራ
የጎንደር ሕብረት —
እነዚህን ፀራ አማራ ናቸው ሲሉ
ከዚህ ባሻገርም በአሁኗ ሰዓት ኢትዮጵያውያን ከሕወሀት ግድያ ከሞት ያመለጡ የሚሸሹበት ጎረቤት ሀገር የለንም ።
ይህ እየታወቀ እነዚህ አማራንገና እናደራጃለን እያሉ ለ25 ዓመት ሲኖሩ ለምን እንዳልተደራጁ ምክንያት የማይሰጡ አማራን በኣራነቱ ገና ልናደራጅ ይሉና ሱሪ በአንገት እንዲሉ መያዣ መገረዣ ያጡ ነገር ግን ትግሉ ከማን ጋር እያደረጉ እንደሆን እያየነው ያለው ከጅምሩ ግልፅ ነው ሕወሀት ከሚሄድበት መንገድ ያልተለየ የሕወሀትን ጠላቶች የአማራ ጠላት ያደረገ አካሄድ ነው
#ከጎረቤት ሀገር ሕወሀት ገብቶ እንደፈለገ የማያደርግባት ሀገር ብትበኖር አንዲት ሀገር ኤርርራ ነች ታዲያ እኒህ የአማራ አደራጅ ነን የሚሉን ኤርትራን ጠላት ሲሉ ምን መሰለት ነው በ ETV እንደምንሰማው ማለት ነው ስለሱዳን ኬንያ ጅቡቴ የሚያነሱት የሚያወሱት ምንም ነገር የለም አያሌ ኢትዮጵያውያንን በነዚህ ሀገራት እየታፈኑ የደረሱበት የማይታወቀውን እረስተውት መሰለኝ ።
በሥም እንኳ ኤርትራ ብለው ለመጥራት የማይደፍሩ መንግሥቷንም መንግሥት ብለው እውቅና የማይሰጡ ብቸኛ የአማራው ተወካይ ነኝ የሚሉት ። ይህ ሁሌም በሕውሀታውያን እየሰማን ከኖረው ያልተለየ አካሄድ አንግበው ነው ።
የንግግራቸው ርዕስ የሚሆነው ልክ እንደ ሕወሀቶች #ሻዕቪያ ሲሉ ይደመጣሉ ።
በኤርትራ ለሚኖሩት ወገኖችም ታሳቢ ያላደረገ ንግግሮችን ያደርጋሉ ታዲያ ይህ አካሄድ ለአማራው ታስቦ ወይስ ሕወሀት የሚጠላውን መጥላት የትግል አማራጭ አዋጭ ሁኖ ነው?
ከሁሉም በላይ ታዋቂ የሆኑ ግለ ሰብ ለአማራው ብዙ የተናገሩ
ከሰሞኑ እንዳሉት
#የአገውን እና #የቅማንትን ማሕበረ ሰብ ሲከሱ ተሰምተዋል ።
ይህ ደግሞ ሕወሀት ሰሞኑን በጎንደር ላይ ቅማንትና አማራ በሚል ለጀመረው የአረንጓዴ መብራት ሆኖ የሚጠቅም ነው ።
ባጭሩ በዚህ መልኩ አማራዊ ትግላችን ከጅምሩ በዚህ አካሄድ መዳረሻው የሚሆነው የሕውሀት ዕቅዶች ያለምንም እንከን እንዲከናወኑ እድሉ በአዲሶቹ የአማራ እንደራጅ ፈሊጥ እየተመቻቸለት መሆኑ ነው ።