ሚያዝያ 30/2016 ዓ/ ም
~~~~~~©~~~~~~~~
የትንሳኤ ዋዜማ ዕለተ ቅዳሜ ወይ ቅዳም ስዑር ።
አንድ አስደንጋጭ ነገር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተመለከትኩ ።
በጣም ደነገጥኩ እስካሁን ከምሰማቸው ነገሮች ሁሉ የከፋ ከባድ ድንጋጤ ነበር ።
ስለ ወጣቱ ‪#‎አባይ‬ ዘውዱ በዕስር ቤት እንዳለ ሕይወቱ አዳጋ ላይ ናት መባሉ ።
ይህ ወጣት ገና የልጅነት ጊዜውን አልጨረሰም ።
አለመታደል ሁኖ በተፈጥሮ ለም የሆነ መሬት ያለበት አካባቢን ለመቆጣጠር የትግራይ ወራሪው ቡድን መሬታቸውን ለመንጠቅ ከደንበር ተሻጋሪ ከሱዳን ጦር ጋር በጣምራ ጥቃት ከሚደርስበት አብራሃጅራ ከተባለው አካባቢ ነው ትውልዱ ።የተማረ ወጣት ነው በተማረው በዕወቀቱ እናት ሀገሩን ለማገልገል ዕድሉ ተነፍጎት ተቀጥሮ ይሰራበት ከነበረው መ/ ቤት ተባረረ ቦዘኔ እንዲሆንም ተደረገ ።
ይህ በመሆኑ በሰላማዊ መንገድ መብቴን አስከብራለሁ ብሎ በሕውሓቱ ሕግ በሚባለው መሰረት ከፖለቲካ ፓርቲ አባል ሁኖ ሕጋዊ ነይ መንቀሳቀስ ጀመረ ።
ከዚህ በኋላ የወጣት አባይ ዘውዱ ሕይወት አዳጋ ላይ ወደቀች ።
ማስፈራራቱ እስራቱ እንግልቱ ቀጠለ ያነን ሁሉ ታግሶ በዛ ደንበር አካባቢ ሕውሓት የሚፈፅማቸውን ሀገር ማፍረስና አማራ ተብለው በተፈረጁት ወገኖቹ ላይ የሚፈፀመውን በደል በሚዲያ ለሕዝብ በማድረስ ላይ ነበር ። እኔም ያወቅሁት በዚህ ሥራው ነበር
በስተመጨረሻ ከአርማጭሆ ተደጋጋሚ አፈና እየተደረገበት ወገን ሆ ብሎ እየወጣ ይከላከሉለት ነበር ሁኖም ግን ሕውሓት ሀገሪቱን የሚመራ ባለብዙ ጦር በመሆኑ ወገኖቹ አባይ ለመከላከል አልቻሉም አባይ ከሌሊት አፈና አላመለጠም ተይዞ ወደማዕከላዊ ከገባ ከዓመት በላይ ቢሆንም ስለአባይ ዘውዱ ምንም የተባለ ነገር የለም ።
ሁሉም በማዕከላዊ ና በቅሊንጦ በዝዋይ የሚታሰሩት የሀገሬ የወገኔ ጉዳይ ያገባኛል ብለው መሰለኝ ስለዚህ የሁሉም ታሳሪ ኬዛቸው ወይም ምክንያታቸው አንድ ሁኖ ሰሰለ ሁሌም የሚነገርላቸው ጓደኛና ጠያቂ ዘመድ ያላቸው ብቻ ናቸው ።
በጣም ያዛዝናል ።
#=====[[[[[[[==]]]]=====#

” በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው ወጣት አባይ ዘውዱ ሕይወቱ አዳጋ ላይ መድረሱ ታወቀ፡፡
—-
ከሰሜን ጎንደር ታፍኖ በቂሊንጦ የስቃይ ማጎሪያ የሚገኘው የቀድሞ ኣንድነት ፓርቲ ኣመራር ወጣት ኣባይ ዘውዱ በእስር ቤት ሕይወቱ ሊያልፍ እንደሚችል በከፍተኛ ሰጋት ላይ ወድቋል፡፡ ኣባይ ዘውዱ በደረሰበት የጉበት እና ጣፊያ እብጠት ሊፈነዳ ሲሆን በተጨማሪም በቲቪ-በከፍተኛ ደረጃ መታመሙ በደረሰን ጥቆማ ዛሬ 22/08 ቂሊንጦ በመሄድ ከራሱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ወጣት ኣባይ ዘውዱ በህመሙ ሰውነቱ ኣልቆ በሰው ተደግፎ እያቃሰተ ማየት ያማል፡፡ የተሟላ ህክምና እንደተከለከለ ኣባይ እንባውን እያፈሰሰ ይናገራል፡፡ ይህ ለመላው ኣገር ወዳድ በተለይ የኣማራ ሕዝብ በዝምታ ተመልክቶ የወጣት ኣባይ ዘውዱ ሕይወት ልናጣው ከቻልን ለኣማራ ሕዝብ ትልቅ ውድቀት ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍል መገንዘብ ያሻል፡፡ ኣባይ ዘውዱ-ሁለተኛ ድግሪውን ከቅርብ ጊዜ በፊት ያጠናቀቀ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት የቆይታውም ቢሆን ከባሕር ዳር ዩንቨርስቲ የማዕረግ ተመራቂ የነበረ ወጣት ምሁር ነው፡፡ ኣባይ ዘውዱ የቀድሞ ኣንድነት ፓርቲ ከተቀላቀለ በኃላ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ከሚሰራበት ቦታ ከማባረር እንስቶ በኣካሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስበት የቆየ ጠንካራ ጓዳችን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይ ለሱዳን ሊሰጥ በታሰበው መሬት ዙሪያ ኣባይ ዘውዱ ከጎንደር ኣዲስ አበባ ድረስ በመምጣት በኣንድነት ፅ/ቤት ሰፊ የዳሰሳ ጥናቱን ካቀረበ ወዲህ በወያኔ አይን እንደገባ ይነገራል፡፡ ለዚህ ጀግና ጓዷችን ኣገር ወዳድ ሊደርስለት ይገባል፡፡ ኣማራ ልጆቹን በዘረኞች እያስበላ የሚኖረው እስከመቼ ነው?
ወጣት አክቲቪስቶች የሚዲያ ኣካሎች በሙሉ ወጣት ኣባይ ዘውዱ የተሻለ ህክምና እንዲሰጠው ግፊት ማድረግ ሕይወቱን መታደግ ግዴታ ኣለበት፡፡ የነቃ ተሳትፎ ያላቸው የኣማራ ተወላጅ የሚደርሰው ዘር የማጥፋት ድርጊት ሊወገዝ ኣምሮ ሊታገሉት የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ሁሉም ወገን ወዳድ ለኣባይ ዘዉዱ ድምፁን ይሰማለት፡፡ ኣማራ ነገ ታሪኩ ሲነገር ሊያፍርበት ይችላል፡፡ ”
Sintayehu Chekol

Shagiz Shagi's photo.