ያደራ እስረኛ
=======================
አደራ የምታስቀምጠው ንብረትክን እንጅ ወገንክን በአደራ አስቀምጥ ተብለህ ስትሰጥ ምን ይሰማሃል ?
ጎንደርን በተመለከት የተቻለኝን ያክል ለመናገር መልዕክት ለማስተላለፍ ከአመታት በፊት ለመግለፅ ሞከርኩ ።
ነገር ግን ጉዳዩን የኔ አለማለት ይሆን ወይም በመዘናጋት ይሆን አላውቅም ።ሰሚ ጀሮ ያገኘሁ አለመሰለኝም ።
ሕውሓት ጎንደርን የሚያይበት ዓይኑ የተለየ ነው ።
ጎንደር ለምትመሰረተው ለታላቋ ትግራይ ለግብዓትነት ለመጠቀም ከዓመታት በፊት ጀምረው ብዙ በደሎችን እየፈፀሙ እንደነበር ምን ለማድረግ እንዳሰቡ ጭምር ለመግለፅ ሞክሬም ነበር ።
በመጀመሪያ ትግራይን ከተከዜ ማዶ ወደ ጎንደር ክልል ዘልቀው አንድ የዞን ክልል ሲወስዱ ያውም ይህ ክልል የትግራይ ምዕራቫዊ ዞን ወይም የልማት ኮሪደር በማለት ይጠሩታል ያኔ እንኳንስ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ ሊለው ቀርቶ የክልሉ ተወላጅ ከሆነው መካከል ነገሩ አልገባቸውም ነበር ብቻቸውን ከፍተኛ መስዋዕት የከፈሉት የወልቃይት የጠገዴ እንዲሁም የፀለምት ነዋሪዎች ብቻ ነበሩ ።
ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ከጎንደር የአማራ ገበሬ ይዞታ እየተቀማ በወረራ ከትግራይ በመጡ አዲስ ሰፋሪ ከግማሽ ሚሊያን በላይ አሰፈሩበት ባጭር ጊዜ የዚያን አካባቢ ዲሞግራፊ ለመቀየር ተቻለ ።
ከትግራይ ወፈሰቲት ሁመራ ወልቃይት ጠገዴ እንዲሰፍሩ የተደረጉት የትግራይ ተወላጀች ተራ አርሶ አደር ሳይሆኑ የጦር ልምድ ያላቸው የቀድሞ ታጋይ የተሰናበቱትን ነበር ።
በላሙሉ ትጥቅ የማዘዣ ጣቢያ ያላቸው በኢትዮጵያውያን በሚሰበሰበውና በብድር ከውጭ ሀገር በሚሰበሰበው ገንዘብ የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረግላቸው የታጠቁት መሳሪያ ከተራ መሳሪያ እስከ ቡድን መሳሪያ መትረጌስና ብሬን እያሉ የሚጠሩትን መሳሪያ ያነገቡ ናቸው ።
አንጡራው የክልሉ ተወላጆት ከሞት ና ከስደት የተረፉት ተገፍተው ከለም መሬት ይዞታቸው ለእርሻ ወደማይመቸው ተራራማ አካባቢ ብቻ እንዲኖሩ ሲደረግ የምትሰጣቸው የበሬ ግንባር የማታክል ብጣሽ መሬት ናት ። የሚገርመው ኢንቨስተር በሚል ቋንቋ ሰፋፊ መሬት ከተቀራመቱት በኋላም ትርፍ ካለ ለነዛ የጎንደር ተወላጆች አይሰጣቸውም ለባለ ሀብት ተብሎ ውሀ እየጠጣ ይቀመጣል ከዛም በላይ የአስተዳደር በደል እንዲፈፅሙ አስገድዶ መድፈር በሴቶች ላይ እንዲፈፅሙ የተመደቡላቸው የትግራይ ተወላጅ የሆኑ አንድም ለነሱ ያደሩ ከርሳሞችን በመጠቀም ነው ።
ግልፅ የሆነ የዘር ማጥፋት ተካሂዶባቸው እያለ እንኳንስ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰሜን ገንደር የአጎራባች አውራጃዎች ትኩረትን አላገኙም ።
ምክንያት የሰሜን ጎንደር መስተዳድር የተመደቡት ሰዎች በተክክል ክልሉን የማይወክሉ ከተለያዩ የዘር ሀረግ ያላቸው አብዛኛዎቹ ከትግራይ ዝርያ ያላቸው ናቸው ።አንድ ሰው በትክክል ክልሉን የሚወክል በአስተዳደር አይሾምም ።
የነዚህን ሰው ወደስልጣን አምጥቶ ማስቀመጥ የክልሉ ተወላጅ ባለመሆናቸው በበታችነት የሚሰቃዩ በራሳቸው የማይተማመኑ በመሆናቸው የሕውሓትን መርሀ ግብር በትክክል ያስፈፅማሉ ።
ጎንደር ከኢትዮጵያ ክልሎች በከፋ አያያዝ ለ25 ዓምስት ዓመት የመከራ የሥቃይና የፍዳ ዘመን ተሸክማ አሁንም አለች ።
ከዚህ በኋላ ወደማይቀረው የጅምላ ጭፍጨፋና የጅምላ ማፈናቀል ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ ።
አብረው የኖሩትን የጎንደር ነዋሪ በቅማንትና በአማራ መካከል ችግር የተፈጠ በማስመሰል ራሱ ሕውሓት ያስታጠቃቸው የቅማንት ሰላማዊ ገበሬዎች እንዲገሉ ካሰማራ በኋላ ራሱ ሕውሓት በፌዳራል ስም አለሁላችሁ በማለት በቅማንት ሕዝብ ድራማ የመጨረሻው ጎንደርን ለአንዴና ለመጨረሻ የፋይናል ጎሉን የቆየ ሕልሙን ለመፈፀም ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ይመስላል ።
ታላቁ የአባይ ግድብ የተባለው እንደ አሰቡት ከሄደ አገልግሎት ከመስጠቱ በፊት አካባውን በታላቋ ትግራይ መካተት እንዳለባት የሕውሓት እግሮች ሁሉ ወደዛው እያመሩ ነው ።
ለምነው ለሱዳን መሬት ለመስጠት የተነሱበትም አንዱ ምክንያት ይህ ነው ።
ለሚፈጠረው ማንኛውም እንቅስቃሴ ከሱዳን ጋር አብረው ለመስራት የጣምራ አስተዳደር የጋራ ዕዝ የሚመራ ወታደር እስከ ማቆም ተደርሷል ።
የጎንደር ነዋሪዎች እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሱዳን ጠረፍ ማሳከር ሲካሄድባቸው የቆየው ሁሉ መነሻው በዛ ከተመደቡት ከሕውሓት ሰዎች በሚቀርብላቸው መመሪያ ነው ።
ስሙ የሱዳን ወታደር ይባል እንጅ የኛዎቹ ሀገር በቀል ኮሎኒያሊስቶች ናቸው ።
ሕውሓቶች በጎንደር ላይ የሚሰሩት ግፍ ለዓመታት ሕመሙ የማይረሳ ለምፁ የማይጠፋ ቁስሉ እያመረቀዘ ለትውልድ የሚተላለፍ ነው ።
በዙ ቤተ ሰብ ፈርሷል ልጆች ያለ ወላጅ ቀርተዋል ባለ ፀጋ የነበሩ ቆርማዳ ድሀ ለማኝ እንዲሆኑ ተደርገዋል ።
ለምን ብሎ መናገር በሰሜን ጎንደር ትግሬን ትጠላለህ ተብለህ በክልሉ ባለሥልጣን ተይዘህ ያደራ እስረኛ ትሆናለህ የሕውሓት ሰዎች መጥተው ወደሚፈልጉት እስኪወስዱህ ድረስ የክስ መዝገብ የለህም የዕስረኛ ቁጥርም አይሰጥህም ።
ይህ ዕጣ የገጠማቸው እስካሁንም መረዶ ለቤተ ሰብ ያልተነገራቸው የሰሜን ጎንደር ገበሬዎች አዕላፍ ናቸው ።
ያደራ ዕስረኛ የሚባል ሰምታችሁ ታውዋላችሁ?
ያደራ እስረኛ መሆን ማለት ከሳሽህ ወይም ፈላጊህ ሕውሓት ነው ማለት ነው።
በብዛት የአርማጭሆ ገበሬ በጎንደር የዕስር ጣቢያ በአደራ ቆይታቸው ታስረው በክልሉ የፖሊስ ጣቢያ አይመረመሩም ስማቸውም አይጠየቅም ።

በተመቻቸው ሰዓት በሌሊት የሕውሓት ሰዎች መጥተው እስኪወስዷቸው እውነትም እንደሰው ሳይሆ የአደራ
ከብት ሁነው ይቆያሉ ።
@የአደራ እስረኛ! !!!!!!!!!!!!
በሰሜን ጎንደር ምዕራባዊ ዳርቻ ያለው ወርቃማ ምድር የኤትዮጵያውያን ታላቅ አለኝታ የነበረ የህዝብ ሀብት የነበረን ነው የትግራይ ብቻ እንዲሆን የተፈለገው ከነሱ የተረፈው የወዳጅ ማውጮ ለሱዳን የሚሰጠው በተለይ ባሁኗ ሰዓት ከአፋር ከወሎ ረሀቡን ሸሽተው እግራቸው እያመራ ያለው ወደዚችው ህውሀት ማሳከር የሚፈጽምባት ተቆርጣ የቀረች ምድር የመተማን አፈር ነው ወ ሁመራ ለግባት ልዩ ፈቃድ ከመቀሌው አስተዳደር ይጠይቃል ሁሙራ ከመግባት አውሮፓ በህገ ወጥ መግባት የቀላል ምክንያት በአካባቢ በቀላሉ ትግርኞ ባለመናገርህ በቀላሉ ተይዘህ የአሸባሪ ታርጋ ይሰጥሀል ከባድ ነው የጥንቷ የጎንደሬዋ ከተማ ሁመራ የጎንደሬ መቀበሪያ ነች ከአማራ የጸዳች ከተማ

Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.