~~እውን አማራ ሞቶ ተቀብሯልን? ~~
©©©©©©©©\\//©©©©©©©
በ12/ 08/2015 ከኢሳት የሬዲዮ ጣቢያ የቀረበልን ዝግጅት በዚህ ዘመን ለማመን የሚከብድ ነገር ግን ዕውን የሆነ ፣ ከናዚ ጀርመኖች በባሰ ፣ በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የሚፈፀም እጅግ ዘግናኝ አረመኔያዊ ተግባር ወደኋላ ሂጀ ከቅድመ ደርግ ውድቀት ጀምሮ እስከ 24 ቱ የሕውሓት የሥልጣን ዘመን በዘር ማጥፋት ሥራ የተፈፀሙትን እንዳስታውስ አደረገኝ ።
— ወገን አንድ ምክር ወይም እርዳታ የሚሰጠኝ ዘመድ እፈልጋለሁ ።
—ወይም እናንተንም እንደኔ ያደርጋችኋል?
— እኔ የምኖረው ከ20 በላይ ከምወዳት ሀገሬ ርቄ ከሀገር ወጥቸ ነው ፣ ግን ለሰዓታት ቀርቶ በየደቂቃዎች ከሀገሬ ጉዳይ ተለይቸ አላውቅም ። ለሚዲያ በጣም ቅርብ ነኝ ። ስለሀገሬ የተፃፉ የተነገሩ አያመልጡኝም ።
— ውድ ወገኖቸ ሀሳብ አካፍሉኝ ገጠመኞቻችሁን ንገሩኝ ሚያበረታታም ነገር ካለ ንገሩኝ ወገን መረዳዳት ካለብ አሁን መሆን አለብን ከዘገየ በኋላ ሁኖ በመቃብር የሚረዳ የሚደረግም አይኖርም ።
— በርግጥ በኔ አዕምሮ ዘወትር መልስ የሚሆን ሀሳብ ይመላለሳል ሁኖም ግን የወገን መተባበር ላይ ያለኝ እይታ ተስፋዬን የሕልም ሩጫ የማይፈታ ሕልም ይሆንብኛል ።
— ምክንያቱን ሳለውቀው የኔ ያልከው ሰው ካንተ ርቆ ይባስም ብሎ የራስህ ሰው አንተን ለመጉዳት ለጋራ ጠላት ለሆኑት መሳሪያና መጠቀሚያ ሁኖ ስታየው ከአምላክ የወረደ እርግማን ያለብን ይመስለኛል ።
ሀቁ ቅርብ እያለ ሀቅን ለመደበቅ ከሕዝብ ጠላቶች ከሚሰጡት በበለጠ መከራከሪያም በላይ ልታሰምናቸው ወይም በማያሳምኑህ ነገር ተጠምደው ጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜህን ይገሉታል ።
:::::::::::——+++++++——;;;::::::::::::::
እኔ የምለው እውነትም ሳሞራ የኑስ አማራን ዳግም እንዳይነሳ ጉድጓድ ምሰን ቀብረነዋል ።
አቶ ስብሐት ነጋ የአማራና የኦሮቶዶክ ዕምነት አከርካሪው ተሰብሯል ፣ብለው የተናገሩት እውነታ የለውምማለትይቻላል ??????????????
ሕውሓት ከቤት እያፈነ ፣ እንደቤት ክዳን እሳር አንዳንድ እያለ ፣እየመዘዘ በስውራ ከማጥፋት ከምሁር እስገበሬ ከሴት እስከወንድ ፆታ ዕድሜ ሳይለይ አሰቃቂ በደሎች ፈፅሟል ።
በግልጽ በማንፌስቶው ሕውሓት ለትግራይ ሕዝብ ብቸኛ ጠላት አማራ ሲል አስቀምጧል ለዚህም ጥናታዊ ስታስቲክስ ያጣቅሳል ።
ለትግራይ ሕዝብ ማነው ጠላትህ ብለን ብንጠይቀው ይሉና ከመቶው ከዘጠና በላይ የሚሆኑት በአንደኛ ደረጃ አማራ ጠላት ነው ብለውናል ይላል ።
አማራ የተነፃፀረው ደግሞ ከወራሪው ከፋሽሽቱ ኢጣሊ ጋር ነበር ።
እንደነሱ አባባል ፋሽብት ኢጣሊ የትግራይ ጠላት አለመሆኑን የሚያሳይ ነበር ።
ወገኔ በሃሳብ እርዱኝ ይህ በወገናችን ላይ አደህይቶ የማዳከም እርምጃ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንጅ እየቀነሰ አልመጣም ።
በናንተ በኩል ምን የሚሰማችኋል? አካፍሉኝ መላ በሉኝ ስል እርዳታችሁን እፈልጋለሁ ።
ብዙን ጊዜ ከሀገር ቤት ያሉ አርሶ አደርች ንብረታቸውን ተዘርፈው በአንድ ቀን ወደምስኪንነት ሲቀየሩ ማየትና መስማት ያለእንቅልፍ ሌሊቶች እንደማሳልፍ ስነግራችሁ የምሬን ነው ።
ከጉራ ፈርዳ ፣ከቤንች ማጅ ዞን ፣ ከጋንቤላ ፣ ከቤሻንጉል ፣ በብዛት ከኦሮሞ ክልል ከጅምላ ግድያ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የሚካሄድባቸው አርሶ አደሮች ናቸው ። ——— ለሕውሓት በምንም መልኩ ስልጣኑን ወይም በጥቅሙ ላይ የሚያመጡበት ሥጋት የሚደቅኑ ሁነው አይደለም በቅናትና በጥላቻ የተመረዘ በመሆኑ ነው ። መለስ በየጊዜው በአሻንጉሊቱ ፖርላማ ቀደም ባሉት ዘመንን የአማራን በደል አንስተው ድምፅ የሚያሰሙ ነበረ በዛን ወቅት መለስ የሚሰማውን ውስጣዊ ደስታ ለሸሽገው የማይችልበት አጋጣሚ እንደነበሩት በዩቱብ እየገባን ማየት እንችላለን ።
እናም ሕውሓት አፈናቀላቸው ብዬ በሙሉ እምነት የምነግራችሁ በእርግጠኝነት ሁኘ ነው ።
ማፈናቀሉ ግድያው የሚፈፀመው ሕውሓት ባስታጠቃቸው ፣በክልሉ ላይ የፈለጉትን በአማሮች ላይ ወንጅል እንዲፈፅሙ የሾማቸው ሕውሓት ነው ።
ሕውሓት በኢትዮጵያ ያለገደብ እንደፈጣሪ ሿሚም ሻሪም አንድ እና አንድ እሱው ብቻ ነው ።
ሌሎች አጋር ድርጅት ከሚባሉት ጋር ያለው ግንኙነት የቀጣሪና የየቀጣሪ ነው ።
ሕውሓት ምን ማድረግ እንደፈለገ ጥቅላይ ሚ/ ር ብሎ የሾመው የሚያውቅ አይመስለኝም ለምን የ
ሕውሓት የሀገሪቱ ና የስልጣን ባለቤትነት ብቻ አደለም የሚሰማው እንደፈጣሪም ነው ራሱን ያስቀመጠው ።
ኦህዴድና ብአዴንን ከቁጥር የምታገቡ የዋሆች እንደምትኖሩ እገምታለሁ ።
ከዚህ ሀሳብ ላልተላቀቃችሁ ብዙ ማስራጃ እቆጥራለሁ ነገር ግን በጭፍን የሚደግፍን በምንም አይነት ማሳመን አትችልም ።
በየትኛውም ክልል አስከፊ የሆነ ሥቃይ በአካባቢው ባለሥልጣን ሲፈፀም ከበስተኋላ ያሉት እነ ተክላይ ፣እነ ገብራይ መሆናቸውን ልንዘነጋው አይገባም ።
ለዚህ መረጃ የሚሆነው የተገኘው የችግሩ ገፈት ቀማሽ ራሳቸውናቸው ምክንያቱም ከሚባረሩበት ቦታ አብረው ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ከሕውሓት መንደር በመጡ ሰዎች ተንኮሉ እንደሚጠነሰስ ያውቃሉና በነገራችን ላይ አማሮች በሚፈናቀሉበት አካባቢ የትግራ አኢንበስተሮች ቅድሜ በቦታው ሰፋፊ መሮቶችን ይሰጣቸዋል። እነዛ የትግራይ ኢንበስተሮች የቤት ሥራቸው ቀድመው በዛ ክልል ይኖሩ በነበሩት የአማራ ገበሬዎች የሚፈናቀሉበትን ቅድመ ሁኔታ ያዘጋጃል ማለት ነው ። በወቅቱ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የአማረኛው ክፍል በዚህ መልኩ ነበር የዘገበው

http://ahref=
እንደምሳሌ ባለፈው አመት በምስራቅ ወለጋና በጋንቤላ በ2006 የዓመቱ መጨረሻ በጳጉሜ ወርህ የጀመረው ማፈናቀልን የመሩት የፀጥታ ሹም የነበሩ የክልሉ ተወላጅ ያለነበሩ እንደሆኑ ከ500 በላይ ሰው በጭካኔ ከነሕይወታቸው ቤት ተዘግቶባቸው የተቃጠሉም የነበረበትን እናስታውሳለን ።
ይህን ጽሁፌን መነሻም መድረሻም ያደረግሁት ኢትዮጵያን ከሚገዛት አካል የሆነ መልስ ይገኛል ብየ ጠብቄ አደለም ከዚህ እልቂትና ማዳከም ከተፈረደበት ወገናችን ጎን ተሰልፈን ድምፅ እንኳ ልሆነው የሚገባን ተግባር መሆኑን ለመጠቆም ነው ።
ለወገን ደራሹ ወገን ነው ።
የዛሬ መቶ ዓመት ነበር የቱርክ መንግሥት በግዛቱ ይኖሩ የነበሩት አርመኖች ጨርሶ ለማጥፋት ሲነሳ የመጀመሪያ ተግባሩ ማፈናቀል ነበር ከዛ በኋላ የጅምላ ግድያ የተገባው ።
በዛን ዘመንም ሆነ በናዚ ጀርመኖች የቅድሚ የዘር ማጥፋት ሲጀመር ሀብትን መውረስ ከሥራ ገበታና ከመኖሪያ ቤት ማፈናቀል የሚበላ የሚጠጣ ማሳጣት ነበር ታዲያ ይህን ምልክት በኢትዮጵያ እየተፈፀመ መሆኑን እንክዳለን? ??
ወይስ እንደ አርመኖች በመቶ ሽህ የሚቀጠር አስከሬኖችን ጎዳና ላይ ማየት አለብን ጀኖሳይድ መፈፀሙን ለማመን ።
ሁሉም አሸባሪ ተብለው ከጎንደር ከጎጃም ተይዘው ወደማዕከላዊ ሲገቡ የሚመረመሩት ከፍተኛ የዘር ጥላቻ ባላቸው የትግራ ተወላጅ ካድሬዎች መሆኑን መከራ ተቀባይ የሆኑት በአንድ ድምፅ የሚናገሩት ነው በአማራ እስረኞች ላይ የሚፈፀመው የዘር ፍሬ ዳግም ዘር እንዳይተኩ የሚደረገው በቃላት የማይገለፁ ግፍ የጋራ ሩካቤ እንደሚፈፀምባቸው ይነገራል ከእስር ወጥተው ራሳቸውን መሆን ያልቻሉ አካላቸው ብቻ ሳይሆን ሜንታል ዲስቶርጅ ሁነው ይቀራሉ ይህ ተግባር በአውሮፓ በናዚ ጀርመኖች ከተገነቡት የጅምላ መግደያ ኮንሰንትሬሽን ካንፕ ይፈፀማሉ