ሞጋችና ተሞጋች የሥልጠና ውሸት !!

<<<<<<<<✘✘✘>>>>>>>>>›>>
የሥልጠና ውሽት: — በኔ እይታ ኢህአዴግ እያልኩ ከምናገር ፣ ሕውሓት እያልኩ መናገር ይቀለኛል ኢሕአዴግ የሚለውን መጋረጃ ሲገለጥ ዓይኑን አፍጦ የሚመጣብን ሕውሓት ነው ።
የውሸቱ መነሻና መድረሻ ሟቹ የሕውሓት መሪና ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስተርነት ይመራ የነበረው አቶ መለስ ዜናዊ ነበር ።
ያሁኖቹ የሕውሓት ባለሥልጣናትና የሌሎች ተለጣፊ ባለሥልጣናት ከመለስ የተቀዳችው ውሸት የራሳቸውን ሳይጨምሩ እንዳለች ከመለስ አፍ ስንሰማት የነበረችውን እንደወረደች ነው የሚጠቀሙት ።
አብዛኛውን ጊዜ ኃይለማርያም ደሳለኝ የመለስን ንግግር ኮፒ አድርጎ ሲናገሩ እንሰማለን ።
ሕውሓት የሚቀያይራቸው ተደራቢ የሚሆኑት ብዙ ካባ ቢኖሩቱም ማንነቱን ሊሸፍኑለት አይችሉም ።
አጋር ድርጅት ብሎ ከአራት ተቧድኖ ኢህአዴግ ብሎ ቢቀርብም ።
※—ከአንዱ ከሕውሓት በላይ እኛ የማናየው አንዱ ፈጣሪ ካለሆነ በስተቀር ከሶስቱ አንዱ ምንም ውኃ የሚቋጥር ዋጋ የሚሰጣቸው እንደቁም ነገር የማይታዩ ራሳቸው በሚኒስተር የተቀመጡት ከአቶ ደሳለይ ኃይለማርም ጀምሮ የባለቤትነት ስሜት እንደሌላቸው ራሳቸው ያውቁታል።
ከአቶ ኃይለማርያም ጠቅላይ ሚኒስተርነት ይልቅ አንድ የሕውሓት ተራ ካድሬ የበለጠ (ኮንፊደንስ ) የባለቤትነት ስሜት አለው ከሕውሓት አባል ውጭ በሆኑት ላይ ማሸማቀቅ ይችላል ።
ወደዋናው መነሻ ነጥቤ ልመለስ
——።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።——
የስልጠና ውሸት በሕውሓት ውስጥ በ25 ዓመታት የተገነዘብናቸው ሀቆች አሉን ፣ ሁሉም የሕውሓት ባለሥልጣናት ወደሚዲያ ሲቀርቡ —★ከአቶ ስብሃት ነጋ★— በስተቀር ሁሉም አንዳይነት እስታይል አላቸው ሁሉም የሚናገሩት በውሸት ላይ መሰረት ያደረገ ነው ።
ውሸቱም በአንድ ዓይነት ሲስተም ስልጠና የተወሰደበት የሚመስል የሚጠቀሙበት ቃላት እንኳ ተመሳሳይ የሚናገሩት ሙሉ በሙሉ ሀሰት መሆኑን እያወቁ በሕዝብ ፊት ሲዋሹ ሀፍረት የማይሰማቸው ሁኖም ስናይ ይህ ደግሞ ከበስተጀርባ የተደበቀ አንድ ነገር መኖሩን ያመለክታል ጥሩ ዋሾ ከሆንክ በሕውሓት ቤት ጥሩ ደረጃህ እንደሚሰጥህ ለድርጅትህ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሠራህ ነገር ይሰማሃል ሕዝቡ የሚደረገው ያያል ይሰማል ሁሌም ባለሥልጣኖችእየዋሹት እንደሆን ያውቃል ግን እነሱ የሚዋሹት በኩራት ነው።
ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖምን በማይበት ጊዜ እኒህ ሰውዬ እድላቸው ሁኖ በዚህ ሥርዓት የመጡ በመሆናቸው እንጅ በተፈጥሮአቸው ስብዕናቸውን ሳይ አፈጣጠራቸው ከሞተው መሪ ጀምሮ በሕይወት ካሉት ጋር ተመሳሳይ አይደለም ።
ዶክተሩ ይዘውት የቀረቡት ውሸት ቢሆንም ወደሕዝብ የመቅረፍ ፍላጎታቸው ግልፅ ይህ ባህርያቸው ከአባይ ፀኃየ ከሥዩም መስን ከደብረ ፅዮን ከአርከበ ዕቁባይ ይለያሉ ።
ዶክተሩ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ምንም መልካም ነገር ባይዙም በፌስ ቡክና በትዊተር ከሕዝ ጋር ይገናኛሉ ።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚ/ ር
ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖምና የ VOA ራዲዮ የአማረኛው ክፍል አገልግሎት ሠራተኛ የሆነችው ጋዜጠኛ ።
መካከል የተደረገ ቃለ ምልልስን ተከታትየው ነበር ።
የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማረኛውን አገልግሎት መከታተል ከጀመርኩኝ ከ30 ዓመት በላይ ሁኖኛል ፣ ገና የግማሽ ሰዓት አገልግሎት በነበረበት ጊዜ ነው ፣ ያኔ የነበረው አቀራረብና አሁን ላይ ያለውን ሳወዳድረው በጣም አዝናለሁ የድሮ ናፋቂ አትበሉኝ እውነቴን ነው ።
አሁን አሁንማ ቢኦኤና ዶች በሌ የሬዲዮ ፕሮግራሞች ልክ በአዲስ አበባ ሁነው የሚሠሩ ያክል ሁነው ይታዩኛል ።
ያኔ በደርግ አገዛዝ ላይ ይደረግ የነበረው ስለት መጥረቢያ ና ሰይፍ ወደአፎቱ ተከቶ በዚያ ፋንታ ልክ በአንድ አንባ ገነን አገዛዝ ሥር እንዳለ የሚዲያ ሥርዓት እውነትን ለመጠየቅ ፈርተው ና ተሸማቀው ሥራቸውን በትክክል እየተወጡ ያሉ አይመስለኝም ።
ይህ የሚያሳየው ከኒህ ምዕራባዊያን ሀገሮች የሚደረግልን ሁሉ እውነታዎቹን የተረዳን አይመስለንም ።
ጋዜጠኛዋ ትዝታ በላቸው ዶክተር ተዎድሮስን በምትጠይቅበት ጊዜ ብዙ እውነታዎች በአይን የሚታዩ በእጅ የሚዳሰሱ ሃቆችን ለዶክተሩ አልጠየቀቻቸውም ።
ስለ ነፃው ምርጫ
ስለዲሞክራሲ በኢትዮጵያ
ሕውሓት ቂመኛ ስለመሆኑ
እነዚህ በመጠኑም ቢሆን አንስታቸው ነበር ።
የቀሩና ያልተነሱ አንኳር የሆኑት የሕውሓት ተግባሮች አልተነሱም ።
ምንም በ25 የሕውሓት አገዛዝ በኢትዮጵያ ያደረሳቸውን ሁሉን መዘርዘር ባይቻልም ።
※ — ስለነፃ ምርጫው ሲነሳ የ2007 ቱ ምርጫን ተከትሎ ወደዕስር የተጋዙት የተቃዋሚን ፓርቲ አመራሮች ፣ የተገደሉትን ፣ ከሥራ የተፈናቀሉትን በሥም እየጠሩ እንደመረጃ ማቅረብ ሲቻል ዶክተሩ ሸፋፍነው እንዲያልፋ እድሉ ተሰጣቸው ።
※— ስለ መቶ በመቶ ማሸነፍም ተነሳና እንዴት መቶ በመቶ ማሸነፍ እንደቻሉ እንዴት መቶ በመቶ ማሸነፍ እንደሚቻል ትምሕርትም የሰጡበት መድረክ ነበር የሚመስለው ።
ዶክተሩ መቶ በመቶ ለማሸነፍ የተጠቀሙት እንደሞዴል ስኮትላንድን ነበር ። ሕውሓት ለሚፈፅማቸው አይን ያወጣ ቅጥፈት የሚጠቅሳቸው ብዙ ሞዴሉች አሉት ጋዜጠኞችን ፣ጦማርያንን ለማሰር የፀረ ሽብር ሕጉን በሞዴልነት የወሰደው ከእንግሊዝና ከአሜሪካ እንደሆን እየነገረን ከርሟል ነገር ግን በአሜሪካና በእንግሊዝ በመንግሥት ሥራዎች ፣ በአስተዳደር ብሉሹነት ፣በመንግሥት አካላት ሙስና የሚመስሉ ነገሮችን የሚያጋልጡ ብዕርተኞች በዚህ ህግ አይታሰሩም ።
ሽብር ማለት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት የሚደርሱ እንጅ ፍትህ ጎደለ ድኃ ተበደለ ስላሉ አሸባሪ ብላ እንጦርጦስ የምትከት ሀገረ ኢትዮጵያን የሚመሩን ባለ ሥልጣናት መድረክ ፈጥሮ የፈለጉትን እንዲናገሩ ማድረግ እውነት የቀድሞው
ቪኦኤ ነው? እሰከማለት ነው የተሰማይ ።
※— ሕውሓት ቂመኛ ነው ወደሚለው። ጥያቄ ስንሄድ —
ዶክቶሩ ቂመኛ አይደለንም ነው መልሳቸው
ዶክተሩ አሉ ቂመኛ ብንሆን ኖሮ ራሳቸው ደርጎች ያደረጉት መልስን እኛ ማድረግ ነበረብን ነበር ያሉት ለዚህም አስረግጠው የተናገሩት ደርግ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበሩትን ባለስልጣን ሁሉንም ጊዜ ሳይሰጥ ነው የረሸናቸው እኛ ግን የደርግን ባለሥልጣን ላይ ያን መሰል ተግባር አልፈፀምነም ነበር ያሉት ።
ዶክተሩ እንደሚያስቡት በደርግ ባለሥልጣን ላይ እርምጃ ባለመውሰዳቸው ርህሩህ እንደሆኑ ነው ያቀረቡት ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕውሓትን በደርግ ባለሥልጣን ላይ የተደረገውን በተቃራኒ ነበር የተመለከተው ።
ለደርግ ባለሥልጣን ላይ በሞት ባይቀጡም ከሞት ባላነስ ተቀጥተዋል ግን ግልፅ ባልሆነ መልኩ ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሥለደርግ ባለሥልጣናት እዝነት ይደረግላቸው ብሎ አልጠየቀም እንዲያውም ለፍርድ ይቅረቡ ነበር በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በኋላ ግን የሕውሓት ሴራዎችን ሲረዳ ደርግ የገደለ ሰውን ነበር ሕውሓቶች ግን አገርን እየገደሉ ሲያይ የደርግን ባለሥልጣን የሚደግፍበት ደረጃ ላይ ነበር ።
አስታውሳለሁ ሕውሓት ኢትዮጵያን በተቆጣጠረበት የመጀመሪያዎቹ አካባቢ የጎንደርን ሕዝብ ሰብስቦ የደርግ ሰለባ ቤተሰቦችን ሰብስቦ የጅምላ መቃብሮችን አስከፍቶ ሰዎች እንደአዲስ በእንባ እንዲራጩ አደረጉ ።
የጎንደር ሕዝብ መላኩ ተፈራ እጁ ተይዞ ጎንደር ላይ ለፍርድ እንደሚቀርብ ቃል ተገባ ።
ሕውሓቶች ይህን ሕዝብ እንደአዲስ ቁስሉን ከከፈቱለት በኋላ ምንም የተደረገ ነገር አልነበረም ሁሉም ተረሳ ።
ይህ ሁኔታ ከሕውሓቶች ማንነት ሕዝቡ የተረዳው ዕውነታ አለ በሥልጣን ላይ ሁነው በሕዝብ ላይ ሰቆቃ የፈፀሙ ሁሉ ተገቢ ቅጣት በሰጥ ኑሮ የአሁኖቹ ለሕውሓቶች ደረጎች ትምህርት ይሰጥ ነበረ ።
እናም ዶክተሩ እንዳሉት ሳይሆን የደርግ ባለስልጣኖች ለሕውሓቶች መንገድ ጠራጊ ስለነበሩ ባለውለታቸውም ነበሩ።
በደርጎች ላይ ብዙም ይህ ነው የሚባል እርማጃ በግልፅ ያልወሰዱበት ምክንያት በሥልጣን ላይ ሁኖ ግፍ በፈፀመ ላይ የሆነ እርምጃ መውሰድ ያልፈለጉበት ነግ ለኔ ያሉ ወይም አሁን በሕዝብ ሰቆቃ እንዲፈፅሙ የሚላኩት አፋኝ ቡድኖችን ነግ ለኔ እንዳይሉ የፈለጉትን ቢገድሉ እንደማይጠየቁ ያሳዩበት ነው ።
የጋዜጠኛዋ የትዝታ ጥያቄ መሆን የነበረበት— —
※—— እሽ ዶክተር ለቀድሞዎቹ ነፍሰ በላዎች ለደርግ ባለ ሥልጣን ለነበሩት ርህራሄ እንዳደረጉ ሲነግሩን
አሁን ላይ ላሉት እስረኞች ታሳሪዎች በአደባባይ የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ፣መብቴን ተነፍጓል ብለው በተናገሩ ከቤት ታፍነው የት እንደገቡ ሳይታወቅ የቀሩ በአደበባይ በጥይትየተደበደቡትን አሁንም በማዕከላዊ እስርቤት ደንቆሮና መሀይማን መርማሪዎች የዘር ጥላቻን በሰነቁ አረመኔዎች ድብደባ የሚካድባቸውን ፣የዘር ፍሬ የሚቀጠቀጥባቸውን ።የውስጥ ሥስ የአካል ክፍላቸውን እንደኩላሊት ማሕፀን የዘር ፍሬና የጡት አካባቢ ተደብድበው ጊዜውን ጠብቆ ለካንሰር የሚዳረጉትንስ ለምንድን ነው ርኅራሄ የማይደረገው? ዕውን ከደርጎች የከፉ ሁነው ነውን?
አወ ለሕውሓት ደርጎች ባለውለታ ብቻም አልነበሩም ደርጎች ተመልሰው ለሥልጣንም አስጊም እንዳልሆኑ ጠንቅቀው ያውቃሉ ።
ሕውሓት በአንዷለም አራጌና በሻለቃ መላኩ ተፈራ ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ ያውቀዋል ያውቀዋል።
መላኩ ተፈራ ዳግም ከሕዝብ ፊት እንደ ማይቆም ያውቃሉ ።
አንዱዓለም ግን የሕዝብ ልጅ ሕዝብ ይከተለዋል ስለተባለ በአስከፊ ሁኔታ ዕድሜውን በእስር ቤት እንዲጨርስ ሲፈርዱ የሕውሓትን ተንኮል እንዲህ አነፃፅራ ጋዜጠኛዋ ብትጠይቅ ነሮ ዶክተሩ ምን እንደሚሆን መልሳቸው ማወቅ ያጓጓን ነበር

Shagiz Shagi's photo.