ጎንደርጎጃም ወሎሸዋ አንድ ነን's photo.

በአማራ ክልል ብቻ እሚካሄድ ሰሞኑኛ ወንጀል
…………………………………………………..
በአማራ ክልል አሁንም ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት እንደቀጠለ ነው። የወያኔ ሎሌዎች በየገጠሩ እየዞሩ አማራውን ጠመንጃችሁን ካላስመዘገባችሁ ማዳበሪያ አታገኙም እያሉ በማስፈራራት አማሮች ሳይወዱ በግድ ጠብመንጃቸውን እያስመዘገቡ ይገኛሉ። ያስቸግራሉ የተባሉትን ደግሞ እየተቀሙ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህም እየተደረገ ያለው ሁለት ነገር ነው፤
1- እንደተለመደው ወያኔ ለአማራው ባለው የማይለውጥ ጥላቻና ንቀት የተነሳና ፤
2- ኮሽ ባለች ጊዜ የተመዘገበውን ጠብመንጃ በየቤቱ ለመልቀም ያመቸው ዘንድ ነው። ወያኔ ሌት ተቀን እንደሚደሰኩረው መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ ካሰፈነ፡ አማራውን ለምን ጠመንጃውን ይቀማል? ወያኔ በትግራይ ህዝብ ላይ የማያደርገውን በአማራው ህዝብ ላይ የመሳሪያ መቀማትና የትጥቅ ማስፈታት ያለምክንያት አይደለም “ጅብ ቀን ቀን የምትደበቀው ለምንድነው ሲሉት፡ ሌሊት ሌሊት የምሰራውን ስለማውቅ ነው” እንዳለው ሁኖበት እንጂ። እና በአማራው ህዝብ ላይ ወያኔ እየሰራው ያለው ጉድ ወይንም ወንጀል እንዳለ ከዚህ በላይ ምን ይኖራል? በነገራችን ላይ ይሄ መሳሪያ ማስፈታት ገንዘብ የሚያስገባ መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ከሁሉም የሚያበሳጨው ግን ለህዝብና ለሀገር ሲል አጥንቱን የከሰከሰን፥ ደሙን ያፈሰሰንና እንደጧፍ የነደደት ህዝብ ማክበር ሲገባ፡ በነፍጠኝነትና በጠላትነት ተፈርጆ ማንም እየተነሳ ሲገድለው፤ ሲሰድበው፤ ሲያንኳስሰውና ሲዘለፈው ቆሞ የሚያይ አማራ ሲገኝ ነው። አማራው ዛሬ ማንም ጎጠኛ እየተነሳ አፉን ሊያፍታታበት የቻለው አማራው ለራሱ ሳይኖር ለሌላው ኖሮ ሳለ አማራውን ወያኔና በወያኔ ብርና ዶላር ገፋፊነት ወረቀት የሚያበላሹ ቅጥረኞቹ ጸሀፊና ጋዜጠኛ በሉኝ ባዮች አማራውን የስህተትና የጥፋት ቋት በማድረግ ለህዝብና ለአገር ያደረገውን አንዳች ነገር እንደሌለ በመካድ ነጋ ጠባ ውንጀላን በመደርደር ዋሾ ቅጥረኛ በመሆናቸው ነው። ከነዚህ ቅጥረኞች በተጨማሪ ተማርን ብለው የአማራን ታሪክ አጣመው በምሁርነት ካባ የሚጽፉ ሆዳሞችም አልጠፉ። እነዚህም ቢሆኑ በጠላትና በፈረንጅ ትምሀርት ቤቶች ገብተው የክህደትና መሀይምነት ዶክተሮች የሆኑ ናቸው። በነገራችን ላይ ወያኔ በአማራ ላይ የሚያደርሰው ሁሉ የጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ አካል ነው። ይህንን ዝም ብሎ የሚያይ የአማራ ልጅ ያልታደለና የተደየነ ብቻ ነው። የወያኔው የእጅ ስራ የሆነው ብዓዴን እንደሆነ የአማራን ህዝብ ከከዱትና ከጠሉት ከራርመዋልና የአማራን ህዝብ ይታደጋሉ ብሎ መጠበቅ ፋይዳ ቢስነት ነው። ብዓዴን ስለአማራ ይሉኝታን ከገደለ ከርሟል። በዚህም የተነሳ ወያኔ ካፈጣጠሩ አንስቶ በብዓዴን ሽፋን የአማራን ህዝብ ከማጥፋት ሌላ ራሱም በቀጥታ ተሰማርቶ ህዝባችንን እየፈጀው ይገኛል። ስለዚህ መላ ያማራ ተወላጅ የሆንህ ሁሉ ቆሻሻውንም ከጫንቃህ ላይ አንሳና ተነሳ። ስለዘርህ ስትል ዛሬውኑ ስርየትንና ንጹህነትን ፈላጊ ሁን። እና በዚህ ያደቆነኝ ሰይጣን ይጨርሰኝ ባዮች በበዙበት አገራችን ውስጥ የህዝባችን መጥፋት የሚቆጭህ ወዲህ በለኝ። የተማርን ነን የምንል የአማራ ተወላጆች ደግሞ የአማራውን ሙሉና ሀቀኛውን ታሪክ እናስተምር! ሁላችንም አማራን ስለመታደግ የምንችለውን ሁሉ እናደርግ ዘንድ ጥሪ አስተላልፍላችኋልችሁ።