@@///@@@ አይ አንች ሀገር @@@//////@@

እስኪ ፍረዱት እነዚህ ሰዎች የሚያሞግሷት የሚቀድሷት የሚያንቆለጳጵሷት ኢትዮጵያ በዜትኛው ፕላኔት የምትገኝ ይሆን ።
ሰላም የሰፈነባት
ፍትህ እኩልነት የተረጋገጠባት
ነፃነት ዲሞክራሲ የሰፈነባት
ሀገረ ኢትዮጵያ አቤት ማስቀናቷ ።
:— እኔ የማውቃት ኢትዮጵያ
:— ሰው በጎሳው እንጅ በችሎታው የሥራ ዕድል የማይገኝባት ።
:— አያት ቅድመ አያታቸው ለዚች አገር ሲሉ የተዋደቁት ታሪክ የሚሻርባት የልጅ ልጆቻቸው ተወልደው ካደጉበት በዘራቸው የሚፈናቀሉባት የሚባረሩባት ሀብት ንብረታቸውን ቤተሰቸውን የሚቀሙባት ።
:—ሰዎች በዘራቸው ተለይተው የሚታሰሩባት የሚገደሉባት ።
:— ጠቅላላ የሀገሪቱ ሀብት ንብረት ፣መንግሥታዊ ተቋማት በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ተያዘባት ።
:— መንግሥት የተባለው ቡድን
ስለዜጎቹ የማይጨነቅባት
ሀገር ዳንበር ሉዓላዊነት የማይከበርባት ሀገር እንደፈለጉ ለፈለጉት ተቆርሶ የሚሰጥባት የራስን የሚጋዛውን ሕዝብ ጠላት ተብሎ የተፈረጀባት ።
ከባዕዳን ጋር ከሕዝብ ተደብቆ የተለያዩ የሀገር ክህደት ውሎች የሚፈፀምባት ።
በታሪክ በባሕል በሀይማኖት ከማይመሳሰሉን አጎራባች ሀገሮች በማበር የራስን ወገን ማስደብደብ የሚፈፀምበት ።

Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.