Islamic State ተብሎ የሚጠራዉ አለም ዓቀፍ የሽብር ቡድን የሰሜን አፍሪካዉ የሊቢያ የቡድኑ ክንፍ በዛሬዉ እለት ክርስቲያ ኢትዩጵያዊንን ወንድሞቻችን 12 ቱን በበርሃ ዉስጥ ዘግናኝ በሆነ መልኩ በጥይት ተደብድበዉ ሲገደሉ ፤16 የሚሆኑ ደግሞ አንገታቸዉን ቀልቶ መግደሉን በዛሬዉ እለት አሳዉቋል፡፡ ይህንንም ልብ የሚነካ ዜና ትላልቅ አለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደ BBC, France 24 , Press Tv, Euro news, Aljazeera እና የተለያዩ የአረብኝ ጣቢያዎችም ዘግበዉታል፡፡ ለእነዚህ ምስኪን ወንድሞቻችን ቤተሰቦች መጽናናትን ይስጥልን፤ እንዲሁም እንዲህ በግፍ ለተገደሉት የወንድሞቻችን ነብስ እግዚአብሄር ይማር ፡፡ አሜን !! በሊቢያ የሚገኙት የቀሪዎች ኢትዩጵያዊያን እጣ ፈንታም አደጋ ዉስጥ ስለሆነ መንግስት በአስቸኳይ ወደ ሃገራቸዉ በፍጥነት የሚመለሱበትን ሁኔታ እንዲያመቻች በኢትዩጵያ ስም እንጠይቃለን፡፡

የእምየ ምኒልክ ልጆች's photo.