ይች ሕፃን ኗሪነቷ በሰሜን ጎንደር በቀደመው አጠራሩ ወገራ አውራጃ በዳባት ወረዳ ጃኖራ ከሚባለው  ሲሆን ሀገር ሰላም ብለው ከመኖሪያ ቤታቸው ሰላማዊ እንቅልፍ ላይ ነበሩ ግን ያች ዕለት ለዚች ሕፃን መለካም አልነበረችም መኖሪያ ቤታቸው በዙሪያው በተኩስ እሩምታ ናዳም ወረደበት የቤቱም ነወሪዎች ተገደሉ የቤት እንሰሳዎችም ጭምር ሞቱ ሕፃኗም እንደምታዩት የቀኙን እጇም  ተቆረጠ የተረገመች ቀን።
ይህን የመሰለው ግድያ በሰሜን ጎንደር አካባቢ በስፋት ይታወቃል የሚፈፀመውም በመንግሥት ታጣቂዎች ነው ።
ለምንድን ነው ተብለው ሲጠየቁ በስሕተት ነው ወይም ሰው አስገብተሀል ወይም መሳሪያ ደብቀሀል ነው መልሱ ።
አስታውሳለሁ በ1985 አካባቢ ይሆናል በዚሁ አውራጃ በገላና ኪንፋዝ በሚባሉት አካባቢ በተደጋጋሚ ይፈፀሙት ነበር ።
በገላ ሮቢት ከምትባል ቦታ ሰውየው የአካባቢ የሸንጎ አባል የነበረ የሽግግር መንግሥት ይባል በነበረበት ወቅት ነው እናም አንድ ቀን በሌሊት ቤቱ ይታፈናል ከዛም ቤቱ በጥይት እሩምታ ይመታል በመመቀጠልም እጅ ስጥ የሚል ድምፅ ከበስተውጭ ይሰማል የቤቱ አበውራም የመንግሥት ተመራጭም በመሆኑ ወንጀል አልሠራሁ በማለት ለመውጣት በዝግጅት ላይ እንዳለ ባለቤቱ አንተ ከመውጣትህ በፊት እኔ ላረጋግጥ ብላ ሚስቱ በሩን ስትከፍት ተኩሰው መቷት ሚስትም በር ላይ ድፍት አደረጓት ።
በሰሜኑ የሀገራችን የሆነ ነገር የሚያጠራጥር ከሆነ ቀድማ የምትወጣው እሴት ናት እሴትን መግደል ማንም አይሞክርም እሴትን መግደል አሰፋሪም ነበር በባሕላችን ።
ለነገሩ በዘመነ ሕውሓት ይህን ኩሩ ሕዝብ ጡት ቆራጭና ብልት ሰላቪ አድርገው ሲስሉት እናያለን እነብሥራ አማረ በፍኖተ ገድሊ መፅሐፉ እነመምሕር ታጋይ ገብረኪዳን ደስታ ።
10371619_10202160141786086_1518263643866624553_n