★ለወገን የቀረበ የነፍስ አድን ጥሪ ★

“ ዳሩ ካልተከበረ መሀሉ ዳር ይሆናል ”
በፀለምት በዋልድባ ፣በወልቃይት በጠገዴ ፣በሰቲት ሁመራ የተጀመረው የመሬት ወረራ የሰውን ሕይወት ያጠፋና የንብረትን ዘረፋንም ያካተተ ነበር ። ይህም የመጨረሻ አለመሆኑን እያየነ ነው

በሰሜን ጎንደር በወገራ አውራጃ አሁንም የወገን ድምፅ ይጣራል ።
ጎንደርና ትግራይ የተፈጥሮ ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥን መሰረት ያደረገ አስተዳደራዊ ክልል ነበረው ።እሱም የተከዜ ወንዝ ሁለቱንም ክፍለ ሀገር ይለያቸው ነበር ።
አሁን ግን ሕውሓት ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በጠቅላላ የኢትዮጵያ መንግሥት ሁኖ እያለ የትግራይ ክልልን ለማስፋት የቆየውን የአማራ ክልልን በመውረር ወደትግራይ አስተዳደር መቀላቀሉ የአደባባይ ምስጢር ነው ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀዋል ነገር ግን ትኩረት ሳይሰጠው 24 ዓመታትን አስቆጥሯል ።
በሰሜን ጎንደር ላይ የሚፈፀመው ደባ ሕውሓት ወደስልጣን ሳይወጣ ጀምሮ ወደክልል ሰርገው እየገቡ ታዋቂ የሆኑ የአርበኛ ቤተሰብ እስከደርግ ባለስልጣን ድረስ እየገደሉ ይመለሱ ነበር በዛን ወቅት እኔም እራሴ አይገባኝም ነበር በኋላ ነገሩ ሲገባኝ አሁንም ከሚሰሩት ጋር ሳነፃፅረው በትክል በዚህ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ለመሆኑ እርግጠኛ ሁኛለሁ ።
በሰሜን ጎንደር ታዋቂ ከሆኑት ግድያ ከተፈፀመባቸው እማስታውዳቸው ።
:- የቀድሞው የወገራ አውራጃ አስተዳዳሪ ሁነው ለአመታት የቆዩ እስከ ንጉሡ ውድቀት የጠገዴው ተወላጅ
ቢትወደድ አዳነ መኮነን ።
:- በደርግ አገዛዝ ወቅት የወገራ አውራጃ አስተዳዳሪ የወልቃይት ተወላጁን አባይ ጎሹን የብዙ ቀን ጉዞ እደርገው ዳባት ከተማ ድረስ ሰርገው በመግባት በ1973 ዓ/ም ግድያ እንደፈፀሙበት አውቃለሁ ።
:- የኪንፋዙን ጀግና አባ ቡላ የሚባለውን ኪንፋዝ ከሚባለው አካባቢ ከመኖሪያ ቤቱ ድረስ በመሄድ ግድያ ተፈፅሞበታል ። በበለሳ ዙይዘሃየ እስከ ሰሀላ በበየዳና በጃናሞራ ያለቁትን ወገን ይቁጠረው
እንደምሳሌ ብየ ጠቀስኩት እንጅ ወገን በየወገኑ ቆጠራ ቢደረግ በሕውሓት የተገደሉ ፣ከቤታቸው ተወስደው ድራሻቸው ጠፍቶ የቀሩ ጎንደሬዎች አያሌ ናቸው ከዚህ መካከልም አዛውንቶች እናት መነኮሳቶች አሉበት ።
አሁንም የአርማጭሆ ገበሬዎች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙን ነው ልንደርስላቸው ባንችልም ላልሰማው በማሰማት ድምጽ እንሁናቸው ።
ሌላው ቢቀር ድምፅ ልናሰማ ይገባል ሰላማዊ ሰዎች እየሞቱ ነው አሁንም ዝምታው ይሰበር ችግሩ የጎንደሬዎች ብቻ አድርገን ካየነው ታላቅ ስህተት ነው ።
የሕውሓቶችን ተግባር በኢትዮጵያ ምድር ላይ አላውቅም የሚል ያለ አይመስለኝም የሁሉንም በር አንኳኩቷል ።
የሰው ልጅ ሀገር ሊኖረው ይገባል ያለሀገር እምነት የለም ፣ያለአገር ያለወገን ኩራት የለም ።
በወልቃይት በጠገዴ ሕዝብ እስካሁን የተፈፀመው የዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ የዘር ማጥፋት ተፈፅሟል አሁንም አላለቀም ለአጎራባች አርሶ አደር ገበሬዎች እየቀጠለ ያለበት ሁኔታ ነው የሰለው ።
ሕውሓት ብዙውን ጊዜታላቅ ወንጀል የሚፈፅመው በዚህ ሕዝብ ላይ በገበሬዎች ላይ ነው በጅምላ ማፈናቀል መሬት ነጥቆ በድህነት እንዲኖሩ ማድረግ ይህ ሕዝብ በራሱ ክልል ይፈናቀላል የራሳቸውን ሕዝብ ይሰፍራል በየትኛውም ክልል ይህ ሕዝብ ይፈናቀላል ከበስተ ጀርባ ያን ቦታ የሚረክቡት በኢንበስተር መልክ ያው አንዳይነት ቋንቋ ተናጋሪ ይሆናል አይተናል በቀድሞው የጎጃም ክ/ሀገር የአሁኑ ቤሻንጉል አይተና በጋንቤል ይህ ሕዝብ ይገደላል ይባረራል በምትኩ ኢነበስተር ባለሀብቶች ከነሱ በሆኑ ሰዎች ይያዛል በከተማም ከመኖሪያ ቤት የህ ሕዝብ የፈናቀላል በቦታው ማን ፎቅ እየሰራ እንዳለ አዲስ አበባ እንደምሳሌ መጥቀስ በቂ ይሆናል ።
ይሕ ሕዝብ ይመለከተኛል ያገባኛል ሀዘኑና መከራው ይሰማኛል የምንል ሁሉ ለማስቆም ድምፅ የምናሰማው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው ።
አሁን በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ እየተዘጋጁ ያሉት የትግራይ ሚሊሻ በሩዋንዳ በቱሲዎች ላይ እልቂት እነደፈፀሙት እነደፈፀሙት የሁቱ ሚሊሻ አይነቶች ናቸው ።
የሀገሪቱ መከላከያ የሚባለው እያየ ሕገወጥ ታጣቂ በሰላማዊ ገበሬ ላይ ጥቃት ሲፈፀም እያየ አያገባኝም ያለበት ሁኔታ የሚያሳየን ከበስተኋል ማን እንዳለ ግልፅ ነው ።
ይህን አሁን እንጅ ነገ አይደለም የምናወግዘው ።
በተለያየ ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያን በደል እየደረሰባቸው ላለው ሕዝብ ድጋፍ ማድረግ አለብን ዓለም እንዲያውቀው የተቃውሞ ሰልፍ ልናደርግ ይገባል ።
ፍትሕ ለግፉዓን
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !

በሚናገሩት ቋንቋ  ብቻ  ሀብት ንብረት ተወርሰው  ያለምንም  መፍትሄ  ከሀገራቸው  የተባረሩ                                                                         644295_452589738155987_958127676_n77024212