ውለታን የማይረሳ ሀገሩን ወዳድ ሕዝብ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ——:— ዮኒ ናታንያው የመብረቁ ጦር አዛዥ የኢንተቤው ጀግና ፣ሥም ከመቃብር በላይ ይኖራል ።
:— ሁሌም የምመኘው ለሀገረ ኢትዮጵያ ሕዝብ የመብቱ ባለቤት ሁኖ ማየት ነው ።
:— ሁለተኛም ይች ታለቅ ሀገር ባለረዥም ታሪክ የሰሩላትን ሁሉ ውለታ የምትመልስ የጀግኖችም ታላቅ ሥራ ለአዲሱ ትውልድ አኩሪ ታሪክ ሁኖ እንዲቀጥልም ምኞቴ ነው ።
በኢትዮጵያ ምድር ለጋራ አገር ብለው የዳር ድንበር አጥር ሊሆኑ ደማቸውን ያፈሰሱ አጥንታቸውን የከሰከሱ ተገቢውን ከብር መሰጠቱ ይቅርና የነዛ ታላቅ ሰዎች ሥምና ዝና ባዕዳን የሚያውቁት ጠላት ሳይቀር የመሰከሩትን በማንቋሸሻ እውነቱን እና ለመልካም ብለው የሰሩትን ወደ የውሽትና የቅጥፈት ታሪክ በማውራት ።
የጀግኖች ልጆች የልጅ ልጆችን በማሳደድ በተቃራኒው ከጠላት ወግነው ሀገራቸውን ክደው ሕዝባቸውን ሲወጉ የነበሩ የነሱ ልጆች የበላይ ፈላጭ ቆራጭ ሁነው ማየቱ በጣም ያማል ።
ነገር ለነገር አነሳሁት እንጅ ለማለት የፈለግሁት አንድ ነገር ነው ።
በመካከለኛው ምስራቅ ለምትገኝ አንዲት ቲንሽየ ብቸኛዋ መሪዋን ሕዝብ የሚሾምባት የሚሽርባት ሀገር ነው ።
ቢንያሚን ናታንያው ። ለአራተኛ ጊዜ ለጠቅላይ መኒሰተርነት ተመርጠዋል ።
እኒህ ሰውየ በሀሳብ የሚደግፋቸውን ያክል የሚቃወማቸውም አለ ።
ሁኖም ግን ውለታ የማይረሳ ሕዝብ መሆኑን ለመግለፅ ፈልጌ ነው የቤንጃሚን ናታንያው ታላቅ ወንድም ዮኒ ናታንያው ኢንተቬ ላይ የታገቱትን እስራኤላውያንን ለማስለቀቅ መብረቁ በተሰኘው ዘመቻ በአዛዥነት የተመራው በዮኒ ናታንያው ነበር ሁኖም የታገቱትን ያለምንም ጉዳት አስለቅቀው የመሩትን ጦር ያለመስዋዕት በድል ቢመለስም በእስራኤል ሕዝብ ልብ የተቀመጠው ዮኒ ግን ለሌሎች ቤዛ በመሆኑ በሕይወት አልተመለሰም በእስራኤል የጦር ኃይል መመሪያ መሰረት አዛዥ ከሚያዘው ጦር ራሱን ማስቀደም ነው ዮኒ ያነን ነበር የፈፀመው ።
የእስራኤል ሕዝብ ውለታ አይረሳም ።
የፅሁፌም መነሻና መድረሻም የጀግኖቻችን ውለታ አንርሳ ሥልጣን የሕዝብ መሆንም አለበት ለማለት ፈልጌ ነው ።
ሕዝብን አሸንፎ ሥልጣን ላይ መቀመጥ አሳፋሪም ነው ።

Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.
Shagiz Shagi's photo.